የህጻናት አገልግሎት

የህጻናት አገልግሎት ክፍል ዋና አላማ ከ2-14 ዓመት ውስጥ ያሉትን ልጆች የእምነት መሰረት መገንባት ነው። በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠው የእሁድ ቀን የሰንበት ትምህርት ልጆቹን በመንፈሳዊ ትምህርት የሚያሳድግ ሲሆን የአገልግሎት ክፍሉ ራዕይ በተጨማሪ በአመት ውስጥ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ልጆችን በመንፈሳዊ ህይወታቸው ለማሳደግና ህብረተሳባቸውን ለማገልገል የሚችሉበትን ልምድና ችሎታን ማጎልበት ነው።

መርህአችን
ልጆች እግዚአብሔርን በማወቅና ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው ተቀብለው ደቀ መዝሙር እንዲሆኑ ማብቃት ለቤተ ክርስቲያን የተሰጠ ተልዕኮ ነው፡ (ማቴ. 28፡19-20) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ልጆች ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው ( ዘዳ 7፡13፣ መዝ 126፡3) ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው ( ዘዳ 7፡13፣ መዝ 126፡3) ልጆች ለዋላጆች በረከቶች ናችው (ዘዳ 28፡4 ና11) ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲያሳድጉ መማር አለባቸው (ዘፀ 12፤26-27 ምሳ 22፤6) ልጆች ለእግዚአብሔር ካላቸው ዋጋ የተነሳ የመንከባከብ ሃላፊነት አለብን (ዕዝ 22፡6) ከልጆች ሰብአዊ ፍጠረትና ባህሪ እንድንማር እግዚአብሔር ይፈልጋል (ማቴ 18:3 ,19:14 ፊሊጵ 2፤15)

አላማችን
የህጻናትና የወጣቶች አገልግሎት አላማው ታላቁን ተልዕኮ (ማቴ. 28፡19) ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን የሚከተሉት 5ቱ ዋናዋቹ ናቸው ሂዱ :እንዴት ወዴት በምን ዘዴ የሚሉትን መመለስ ያስፈልጋል ደቀመዝሙር ፡በምን አይነት ፈላጎታቸው ነው ወደ ክርሰቶስ የምናመጣቸው እያጠመቃችሁአቸው ፡እንዴት አንድን ልጅ በግል ራሱን ለጌታ እንዲሰጥ መምራት የምንችለው። እያስተማራችሁአቸው: በዚህ ዘመን ያሉ ልጆችን አንዴት ነው በፍላጎታቸው በማስተማር እና በማነቃቃት ዕምነታቸውን ማሳደግ የሚቻለው? ያዘዝዃቸውን ሁሉ እንዲጠብቁ፡ እንዴት ነው ልጆችን ጌታን የሚከተሉና የሚታዘዙ ሌሎችንም የሚማረኩ ማድረግ የሚቻለው?

ግባችን
ተቀዳሚው ግባችን ምንድን ነው? የስራችን መካከለኛ ክርሰቶስ ነውን? ምን ያህል ህጻናትንና ወጣቶች ለመድርስ እንፈልጋለን? ምን አይነት ፕሮግራም ነው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የልጆችን መንፈሳዊና ህበረተሰባዊ ዕድገት ሊያመጣ የሚችለው? የህጻናትና የወጣቶች አገልግሎት ክፍል የልጆችን ሚዛናዊ የሆነ መንፈሳዊ ዕድገት ለመጠበቅ አራቱን አበይት የምግብ ክፍሎችን ያካትታል የመመገብ ፍለጎት ከፋች : በጨዋታ መልክ ልጆችን ሁሉ መድረስ የዳቦ ክፍል : ልጆች በደረጃቸው ያላቸውን ፍላጎትና ችሎታ በመጠቀም ለክርቶስ ቤተ ክርስቲያን የሚያውሉበትን እድል ማዘጋጀት የአትክልት ክፍል: የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለልጆች መሰረታዊ የእምነት እድገት ይረዳል የስጋ ክፍል: ልጆች የአገልግለት እድል ማግኘታቸው የመሪነት ችሎታቸውን ለማሳደግ ይረዳል