እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን

የንባብ ክፍል

‹‹ ያቤጽም። እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው እጅህም ከእኔ ጋር ትሁን እንዳያሳዝነኝም ከክፋት ጠብቀኝ ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው። ›› (1ኛ ዜና 4፤ 10)

ያቤጽ የጸለየው ፀሎት

ባርከኝ

አገሬን አስፋ

እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን

ከክፉት ጠብቀኝ

ለመባረክ፤ ከክፉ ለመጠበቅ፤ ለመስፋት የሚያስፈልገን የጌታ እጅ ነው!!

         እጅህ ከእኔ ጋር ትሁን ስንል ምን ማለታችን ይሆን?

1. ብቃታችን አንተ ነህ

‹‹ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤ እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።›› (2 ቆሮ 3፡5-6)

እጅህን አንሳ -› እኔ እችላለሁ

እጅህ በላዪ ትሁን -› ብቃት የለኝም ካለ አንተ ምንም ማድረግ አንችልም!

2. በሁሉ ያንተ መገኘት ያስፈልገኛል

‹‹ የእግዚአብሔር እጅ ጠንካራ እንደሆነች የምድር አህዛብ ሁሉ እንዲያውቁ አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ለዘላለሙ እንድትፈሩ ነው ›› (ኢያሱ 4፡24)

በመገኘቱ ሰራውን ሁሉ ያውቁ ዘንድ መፈራቱ በሁሉ ይሆን ዘንድ

3. መንፈስ ቅዱስ ይስራ

‹‹የጌታም እጅ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤ ቍጥራቸውም እጅግ የሚሆን ሰዎች አምነው ወደ ጌታ ዘወር አሉ።›› (ሐዋ ስራ 11፡ 21)

የጌታ እጅ ፡ ወንጌል ለመስበክ ፤ ታስፈልጋለች

ወንጌል -› ነጻ ያወጣል፤ ህይወትና ተስፋን ይሰጣል

4. ፈራጅ ነህ (ትበቀላለህ)

ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ላይ ብታምፁ፥ በእናንተና በንጉሣችሁ ላይ የእግዚአብሔር እጅ ትሆናለች። ›› (1ኛ ሳሙ 12፤15)

አመጸኛውን ይቀጣል ከክፋ ስራቸውም ይመልሳል አመጽና አለመታዘዝ ፅዋ አለው ….. ኢሳ 51፤17

5. ብርታቴ ነህ

‹‹እኔም በላዬ ባለችው በአምላኬ በእግዚአብሔር እጅ በረታሁ ከእኔም ጋር እንዲወጡ ከእስራኤል ዘንድ አለቆችን ሰበሰብሁ።›› (ዕዝራ 7፤27-28)

የጌታ እጅ ኃይልና ጉልበት ነው ያጸናል (ያቆማል) ፀሎትህ(ሽ) ምንድን ነው? የጌታ እጅ ከአንተ(ቺ) ጋር ይሁን !!!

Sunday, January 6, 2013
ጌታቸው ወልደየስ