እምነታችን
የህያው ቃል ቤተ ክርሰቲያን ተልዕኮ ወንጌልን መስበክና መኖር ሲሆን ቤተክርስቲያንም በኢየሱስ ክርሰቶስ ፀጋና ዕውቀት የምታድግ የእግዚአብሄር መንፈስና እውነት የሚመራት የአማኞች አካል እነደሆነች የእውነትን ቃል በማመንና በመከተል ፀንታ ትቆማለች።
እግዚአብሔርን መውደድ እና እርስ በራስ መዋደድ የሚገለጡት በጸሎት ፣ በኅብረት ፣ መጻሕፍ ቅዱስን በማጥናት ፣ በማካፈል እና ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ ነው ፡፡ (ሥራ 2 ፡42)
እኛ የሕያው ቃል ቤተክርስቲያን በኦታዋ አማኞች እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን፦ ከሁሉ አስቀድመን በጌታችንና በመዳኅኒታችን በእየሱስ ክርስቶስ ስም የከበረ ሠላምታችንን እናቀርባለን፤ ዘወትር እሁድ ከቀኑ 4፡00 (ፒኤም) በሚኖረን ያምልኮ ጊዜ በመገኘት አብረውን ጌታን እንዲያመልኩ እንጋብዝዎታለን::
እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው. ሮሜ 10:17
ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤ ዕብ 6:19
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ዮሐ 3:16
የህያው ቃል ቤተ ክርሰቲያን ተልዕኮ ወንጌልን መስበክና መኖር ሲሆን ቤተክርስቲያንም በኢየሱስ ክርሰቶስ ፀጋና ዕውቀት የምታድግ የእግዚአብሄር መንፈስና እውነት የሚመራት የአማኞች አካል እነደሆነች የእውነትን ቃል በማመንና በመከተል ፀንታ ትቆማለች።
የሕያው ቃል ቤተ ክርስቲያን ያላትን ራዕይ ለማከናወን የተለያዩ ያገልግሎት ዘርፎችን በማደራጅት ወንጌልን ለሁሉ ለማሰራጨት፤ እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር ለማሳየትና ከጌታ የተሰጣትንም ተልእኮ ለመወጣት ትተጋለች። (ማቴ 28፡20 )
ምእመናን በመንፈስ የሆነ እውነተኛና ትርገም ያለው ህብረት በማድረግ ጌታን እንዲያመልኩና ህብረተሰባችን በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ወደ ጌታ እንዲመጡ መድረስ ነው
ነፍሶችን በክርስቶስ እንዲያምኑ ማሸነፍ (ማርቆስ 16 15)
በማንኛውም የቤተክርስቲያናችን አገልግሎት ወይም በአገልግሎት እንቅስቃሴ ውስጥ ይቀላቀሉን! የሚያድገው የቤተሰባችን አንድ አካል ይሁኑ!
እናመሰግናለን
ሕያው ቃል ቤተ ክርስትያን
የአምልኮ ስፍራ:
2784 Cedarview Rd, Nepean, ON K2J 1A0
የፖስታ አድራሻ:
P.O.Box 34007 Nepean Ontario K2J 5B1
ኢሜል አድራሻ:
colw[at]churchoflivingwordottawa[dot]com
የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ግዜ፡
እሮብ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥናት ግዜ 6፡30 -7፡30 ፒኤም
የእሑድ አምልኮ ግዜ 4፡00 - 5፤30 ፒኤም
Copyright © 2024. All rights reserved COLWIO.