የሕያው ቃል ቤተ ክርስቲያን ያላትን ራዕይ ለማከናወን የተለያዩ ያገልግሎት ዘርፎችን በማደራጅት ወንጌልን ለሁሉ ለማሰራጨት፤ እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር ለማሳየትና ከጌታ የተሰጣትንም ተልእኮ ለመወጣት ትተጋለች። (ማቴ 28፡20 )

መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
መጽሐፍ ቅዱስን በቡድን ማጥናት ህይወትን ይቀይራል እንዲሁም አንዱ ከሌላው ጋር እና ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ያሳድጋል ፡፡
አምልኮ
የሕያው ቃል ቤተ/ክ የአምልኮ ቡድን አምልኮን በመምራት፡ ጉባኤውን ለአምልኮ በማነሳሳት፡ ለእግዚአብሔር የሚገባውን የምስጋና ዝማሬን በማምጣት በእሁድ መደበኛ የአምልኮ ጊዜና አንዲሁም በልዩ መንፈሳዊ ስብሰባዋች ላይ አገልግሎትን ይሰጣሉ።.

ልማታዊ ሥራ
በውስጥና በውጭ ልዩ ልዩ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የህብረተስብ ክፍሎችን ለይቶ መርዳት

ሚድያ
የቤተክርስቲያናችንን የወንጌላዊ ተልዕኮ ለማሳደግ የሚድያ አገልግሎት የማኅበረሰባችንን ሥነምግባር እና መንፈሳዊ ህይወትን የሚያነቃቁ የተለያዩ የቅዱሳት ጽሑፋዊ ቁሳቁሶችን ያቀርባል ፡፡