እምነታችን

Our Faith

የህያው ቃል ቤተ ክርሰቲያን ተልዕኮ ወንጌልን መስበክና መኖር ሲሆን ቤተክርስቲያንም በኢየሱስ ክርሰቶስ ፀጋና ዕውቀት የምታድግ የእግዚአብሄር መንፈስና እውነት የሚመራት የአማኞች አካል እነደሆነች የእውነትን ቃል በማመንና በመከተል ፀንታ ትቆማለች።

  1. ቅዱሳት መጻህፍት፡ መጽሀፍ ቅዱስ 39 የብሉይና 27 ያዲስ ኪዳን መጻሕፍትን የያዘ ቅዱስ፤ ህያውና የእውነት መሰረት መሆኑን፤ እግዚአብሄር ለሰው ደህንነት ይሆን ዘንድ ራሱን በሙላት የገለጠበት ፡ሙሉ ስልጣን ያለው በእግዚአብሄር መንፈስ በተመሩ ሰዎች እንደተፃፈ እናምናለን
  2. ቅዱስ ስላሴ፡ ህያውና እውነተኛ በሆነ፤ ቅዱስ፤ አፍቃሪ፡ ዘላለማዊ፡ ያልተወሰነ፡ ጥበብና መልካምነትን የተሞላ፤ የሁሉ ፈጣሪ በሆነ በአንድ እግዚአብሄር እናምናለን። በዚህ አንድነት ውስጥ በተገለጠ በማለኮት ባህሪው፡ በዘላለማዊነት ስልጣን አንድ በአካል ግን ስስት በሆነ በህያውና እውነተኛ አምላክ በእግዚአብሄር አብ፤ በእግዚአብሄር ወልድ ፤ በእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን።
  3. እግዚአብሄር አብ : ስማይና ምድርን፤ በምድርና በጠፈርም ሁሉ ያሉትን የፈጠረ ፡ መንግስቱ የማይሻር፡ ሁለን የሚያውቅ ዘላለማዊ አምላክ እንደሆነ እናምናለን
  4. እግዚአብሄር ወልድ : ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሄር በእርሱና ለእርሱ ሁሉን የፈጠረበት በመጀመሪያም በእግዚአብሄር ዘንድ የነበረ ቃል ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ የተጸነሰ፤ ከድንግል ማርያም የተወለደ፡ ሐጢያት በማያውቀው ህይወቱ በታምርቱና በትምህቱ እግዚአብሄርን ያሳየ፤ ፍጹም ስውና ፍፀም አምላክ የሆነ አነድያ የእግዚአብሄር ልጅ እነደሆነ፤ አዳኝነቱም በትንቢት እነደተነገረ ለሰው ልጆች ሐጢያት በመስቀል ላይ ቤዛ ሆኖ የሞተ፤ የተቀበረ፤ በሶስተኛው ቀንም ከሞታን በስጋ የተነሳ፤ ወደሰማይ ያረገ፤ አሁን በእግዚአብሄር ቀኝ ተቀምጦ ስለ እኛ የሚማልድ፡ የነገስታት ንጉስ የጌቶችም ሁሉ ጌታ የሆነ፡ መንግስቱንም በጽድቅ ሊያቆም በታላቅ ክብር በግልጽ እየታየ ዳግመኛ የሚመለስ እንደሆነ እናምናለን።
  5. እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ: እንደ ክርሰቶስ የተስፋ ቃል ለቤተክርስቲያን የተላከ አጽናኝ፤ የተሀድሶ ምንጭ፡ለወንጌል ስራ የሚጠቅሙትን የጸጋ ስጦታዋች ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጥ፡ በአማኞ ልብ አድሮ ወደ ንስሀ የሚመራና የንስሀ ፍሬና ለውጥን በአማኞች ሕይወት እንዲኖር የሚረዳ፤ ሰውን ወደ እውነት እየመራ ወደ ደህንነት የሚያደርስ፤ አለምን ስለ ሐጢያትና ሰለፍርድም የሚወቅስ አምላክ እንደሆነ እናምናለን።